ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 16:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. መላው የእስራኤል ማኅበር ከግብፅ በወጡ በሁለተኛው ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን ከኤሊም ተነሥተው በኤሊምና በሲና መካከል ወደምትገኘው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ።

2. በምድረ በዳውም መላው ማኅበር በሙሴና በአሮን ላይ አጒረመረሙ።

3. እስራኤላውያንም እነርሱን እንዲህ አሏቸው፣ “በሥጋ መቀቀያው ምንቸት ዙሪያ ተቀምጠን የፈለግነውን ያህል ምግብ መመገብ በምንችልበት በግብፅ ሳለን፣ ምነው በእግዚአብሔር (ያህዌ) እጅ ሞተን ባረፍነው ኖሮ! እናንተ ግን ይህ ሁሉ ጉባኤ በራብ እንዲያልቅ ወደዚህ ምድረ በዳ አመጣችሁን” አሏቸው።

4. ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን አለው፤ “ከሰማይ እንጀራ አዘንብላችኋለሁ። ሕዝቡም በየቀኑ እየወጡ ለዕለት የሚበቃቸውን ይሰበስቡ፤ በዚህም ትእዛዛቴን ይጠብቁ እንደሆነ እፈትናቸዋለሁ።

5. በስድስተኛው ቀን በሌሎቹ ዕለታት ከሚሰበስቡት እጥፍ ሰብስበው ያዘጋጁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 16