ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 23:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የሐሰት ወሬ አትንዛ፤ ተንኰል ያለበትን ምስክርነት በመስጠት ክፉውን ሰው አታግዝ።

2. “ክፉ በማድረግ ብዙዎችን አትከተል፤ በሕግ ፊት ምስክርነት ስትሰጥ፣ ከብዙዎቹ ጋር ተባብረህ ፍትሕ አታጣምም።

3. በዳኝነት ጊዜ ለድኻው አታድላ።

4. “የጠላትህ በሬ ወይም አህያ ሲባዝን ብታገኘው ወደ እርሱ መልሰው።

5. የሚጠላህ ሰው አህያ፣ ጭነት ከብዶት ወድቆ ብታየው ርዳው እንጂ ትተኸው አትሂድ።

6. “በዳኝነት ጊዜ በድኻው ላይ ፍርድ አታጓድልበት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 23