ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 33:18-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ከዚያም ሙሴ “እባክህ፤ ክብርህን አሳየኝ” አለው።

19. እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “መልካምነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ በፊትህም ስሜን እግዚአብሔርን (ያህዌ) ዐውጃለሁ፤ ለምምረው ምሕረት አደርጋለሁ፤ ለምራራለትም ርኅራኄ አደርጋለሁ፤

20. ነገር ግን፣ ማንም እኔን አይቶ መኖር ስለማይችል፣ ፊቴን ማየት አትችልም።

21. ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “በአጠገቤ ስፍራ አለ አንተም በዐለት ላይ ትቆማለህ፤

22. ክብሬ በዚያ ሲያልፍ በዐለቱ ስንጥቅ ውስጥ አደርግሃለሁ፤ በዚያም እስከ ማልፍ ድረስ በእጄ እጋርድሃለሁ፤

23. ከዚያም እጄን አነሣለሁ፤ ጀርባዬንም ታያለህ፤ ፊቴ ግን መታየት የለበትም።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 33