ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 13:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አብራም ሚስቱንና ንብረቱን ሁሉ ይዞ ከግብፅ ወደ ኔጌብ ሄደ፤ ሎጥም አብሮት ነበረ።

2. አብራም በከብት፣ በብርና በወርቅ እጅግ በልጽጎ ነበር።

3. አብራም ከኔጌብ ተነሥቶ እስከ ቤቴል ተጓዘ፤ ቀድሞ በቤቴልና በጋይ መካከል ድንኳኑን ከተከለበት፣

4. ለመጀመሪያ ጊዜም መሠዊያ ካቆመበት ስፍራ ደረሰ፤ በዚያም የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም ጠራ።

5. ከአብራም ጋር አብሮት ይጓዝ የነበረው ሎጥ በጎች፣ ከብቶችና ድንኳኖች ነበሩት።

6. ሆኖም ሁለቱ አንድ ላይ ሲኖሩ ስፍራው አልበቃቸውም፤ ንብረታቸው እጅግ ብዙ ስለ ነበር፣ አብረው መኖር አልቻሉም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 13