ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 15:17-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ፀሓይ ገብታ ከጨለመ በኋላ የምድጃ ጢስና የሚንበለበል ፋና ታየ፤ በተከፈለውም ሥጋ መካከል ዐለፈ።

18. በዚያ ዕለት እግዚአብሔር (ያህዌ) ለአብራም እንዲህ ሲል ኪዳን ገባለት፤ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤

19. የምሰጣቸውም የቄናው ያንን፣ የቄኔዛውያንን፣ የቃድሞናውያንን፣

20. የኬጢያውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የራፋይምን፣

21. የአሞራውያንን፣ የከነዓናውያንን፣ የጌርጌሳውያንንና የኢያቡሳውያንን ምድር ነው።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 15