ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 23:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ኬጢያዊው ኤፍሮንም እዚያው መካከላቸው ተቀምጦ ስለ ነበር፣ ወደ ከተማው በር መግቢያ መጥተው የተሰበሰቡት ኬጢውያን በሙሉ እየሰሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤

11. “እንዲህ አይደለም ጌታዬ፤ አድምጠኝ፤ ዕርሻውን በውስጡ ካለው ዋሻ ጋር ውሰደው፤ እነሆ፤ በወገኖቼ ኬጢያውያን ፊት ሰጥቼሃለሁ፤ ሬሳህን ቅበርበት።”

12. አብርሃም እንደ ገና የአገሬውን ሕዝብ እጅ ነሣና

13. ሁሉም እየሰሙት፣ የዕርሻውን ቦታ ዋጋ ልክፈል፤ እባክህን ተቀበለኝና ሬሳዬን ልቅበርበት” አለው።

14. ኤፍሮንም ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 23