ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 29:2-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እዚያም በአንድ ሜዳ ላይ ሦስት የበግ መንጋዎች ተኝተው በነበሩበት አጠገብ የውሃ ጒድጓድ አየ። የበግ መንጋዎቹ የሚጠጡት ከዚሁ ጒድጓድ ሲሆን፣ የጒድጓዱም አፍ ትልቅ የድንጋይ መክደኛ ነበረው።

3. መንጎቹ ሁሉ በጒድጓዱ አጠገብ በሚሰበሰቡበት ጊዜ፣ እረኞች ድንጋዩን ያንከባልሉና በጎቹን ውሃ ያጠጣሉ፤ ከዚያም ድንጋዩን በቦታው መልሰው የጒድጓዱን አፍ ይገጥሙታል።

4. ያዕቆብም እረኞቹን፣ “ወንድሞቼ፤ ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው።እነርሱም፣ “ከካራን ነን” አሉት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 29