ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 3:14-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) እባብን እንዲህ አለው፤ “ይህን ስለ ሠራህ፣“ከከብቶችና ከዱር እንስሳት ሁሉተለይተህ የተረገምህ ሁን፤በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ በደረትህእየተሳብህ ትሄዳለህ፤ዐፈርም ትበላለህ።

15. በአንተና በሴቲቱ፣በዘርህና በዘሯ መካከል፣ጠላትነትን አደርጋለሁ፤እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤አንተም ተረከዙን ትቀጠቅጣለህ።”

16. ሴቲቱንም እንዲህ አላት፤“በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤በሥቃይም ትወልጃለሽ፤ፍላጐትሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤እርሱም የበላይሽ ይሆናል።”

17. አዳምንም እንዲህ አለው፤ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ፣ ‘ከእርሱ አትብላ’ ብዬ ያዘዝሁህን ዛፍ በልተሃልና፣“ከአንተ የተነሣ ምድር የተረገመች ትሁን፤በሕይወትህ ዘመን ሁሉምግብህን ጥረህ ግረህ ከእርሷ ታገኛለህ።

18. ምድርም እሾኽና አሜከላታበቅልብሃለች፤ከቡቃያዋም ትበላለህ።

19. ከምድር ስለ ተገኘህ፣ወደ መጣህበት መሬት እስክትመለስድረስእንጀራህን በፊትህ ላብ ትበላለህ፤ዐፈር ነህናወደ ዐፈር ትመለሳለህ።”

20. አዳምም የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና ሚስቱን ሔዋን ብሎ ጠራት።

21. እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ከቈዳ ልብስ አዘጋጅቶ አዳምንና ሚስቱን አለበሳቸው።

22. ከዚያም እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም)፣ “ሰው መልካምንና ክፉውን ለይቶ በማወቅ ረገድ አሁን ከእኛ እንደ አንዱ ሆኗል፤ አሁን ደግሞ እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ቀጥፎ እንዳይበላ፣ ለዘላለምም እንዳይኖር ይከልከል” አለ።

23. ስለዚህ የተገኘበትን ምድር እንዲያርስ፣ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሰውን ከዔድን የአትክልት ስፍራ አስወጣው፤

24. ሰውንም ካስወጣው በኋላ፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በየአቅጣጫው የምትገለባበጥ ነበልባላዊ ሠይፍ ከዔድን በስተ ምሥራቅ አኖረ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 3