ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 36:14-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. የፅብዖን የልጅ ልጅ፣ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት አህሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ፤

15. ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ስፎ፣ አለቃ ቄኔዝ፣

16. አለቃ ቆሬ፣ አለቃ ጎቶምና አለቃ አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ።

17. የዔሳው ልጅ ራጉኤል ልጆች፦አለቃ ናሖት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሣማና አለቃ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጅ ነበሩ።

18. የዔሳው ሚስት የአህሊባም ልጆች፦አለቃ የዑስ፣ አለቃ የዕላማና፣ አለቃ ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ፣ ከዔሳው ሚስት ከአህሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ።

19. እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ።

20. በዚያች ምድር ይኖሩ የነበሩ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣

21. ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 36