ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 36:29-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. የሖሪውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣

30. ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።

31. ንጉሥ በእስራኤል ከመንገሡ በፊት፣ በኤዶም የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ነበሩ፦

32. የቢዖር ልጅ ባላቅ በኤዶም ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።

33. ባላቅ ሲሞት፣ የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በምትኩ ነገሠ።

34. ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማኒው ሑሳም በምትኩ ነገሠ።

35. ሑሳም ሲሞት፣ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ምድር ድል ያደረጋቸው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዓዊት ይባል ነበር።

36. ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።

37. ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኦል በምትኩ ነገሠ።

38. ሳኦል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን በምትኩ ነገሠ።

39. የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፋዑ ይባል ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣብኤል ሲሆን፣ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት ነበረች።

40. ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 36