ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 36:34-43 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማኒው ሑሳም በምትኩ ነገሠ።

35. ሑሳም ሲሞት፣ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ምድር ድል ያደረጋቸው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዓዊት ይባል ነበር።

36. ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።

37. ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኦል በምትኩ ነገሠ።

38. ሳኦል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን በምትኩ ነገሠ።

39. የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፋዑ ይባል ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣብኤል ሲሆን፣ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት ነበረች።

40. ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣

41. አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፊኖን፣

42. ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣

43. መግዲኤልና ዒራም፤ እነዚህ፣ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው ከኤዶም የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ።ይህም ዔሳው፣ የኤዶማውያን አባት ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 36