ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 4:23-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ላሜሕ ሚስቶቹን እንዲህ አላቸው፤“ዓዳና ጺላ ሆይ ስሙኝ፤የላሜሕ ሚስቶች ሆይ አድምጡኝ፤አንድ ሰው ቢያቈስለኝ፣ጒልማሳው ቢጐዳኝ፣ ገደልሁት፤

24. ቃየንን የሚገድል ሰባት ጊዜ ቅጣት ካገኘው፣የላሜሕ ገዳይማ ሰባ ሰባት ጊዜ ቅጣት ያገኘዋል።”

25. አዳም እንደ ገና ሚስቱን ተገናኛት፤ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። “ቃየን በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር (ያህዌ) ምትክ ሰጠኝ” ስትል ስሙን ሴት ብላ ጠራችው።

26. ለሴትም ደግሞ ወንድ ልጅ ተወለደለት፤ ስሙንም ሄኖስ አለው።በዚያም ዘመን ሰዎች የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም መጥራት ጀመሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 4