ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 47:28-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. ያዕቆብ በግብፅ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ዕድሜውም አንድ መቶ አርባ ሰባት ዓመት ነበር።

29. እስራኤልም የሚሞትበት ጊዜ መቃረቡን እንደ ተረዳ ልጁን ዮሴፍን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “በአንተ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ እጅህን በጭኔ ላይ አኑረህ፣ በጎነትንና ታማኝነትን ልታደርግልኝ ቃል ግባልኝ፤ በምሞትበት ጊዜ በግብፅ አትቅበረኝ፤

30. እኔም ከአባቶቼ ጋር ሳንቀላፋ፣ ከግብፅ አውጥተህ እነርሱ በተቀበሩበት ቦታ ቅበረኝ።”ዮሴፍም፣ “እሺ፣ እንዳልከኝ አደርጋለሁ” አለ።

31. ያዕቆብም፣ “በል ማልልኝ” አለው። ዮሴፍም ማለለት፤ እስራኤልም በዐልጋው ራስጌ ላይ ሆኖ ጐንበስ አለ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 47