ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 49:2-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. “እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤ተሰብሰቡና ስሙ፤አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ፤

3. “ሮቤል፣ አንተ የበኵር ልጄ ነህ፤ኀይሌና የጒብዝናዬም መጀመሪያ፤በክብር ትልቃለህ በኀይልምትበልጣለህ።

4. እንደ ውሃ የዋለልህ ነህና እልቅናአይኖርህም፤የአባትህን መኝታ ደፍረሃል፤ምንጣፌንም አርክሰሃል።

5. ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች፣ሰይፎቻቸው የዐመፅ መሣሪያዎች ናቸው።

6. ወደ ሸንጎአቸው አልግባ፤ጉባኤያቸው ውስጥ አልገኝ፤በቍጣ ተነሣሥተው ሰዎችን ገድለዋል፤የበሬዎችንም ቋንጃ እንዳሻቸው ቈራርጠዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 49