ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 49:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. “አንተ የአንበሳ ደቦል ይሁዳ፤ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ በምድርም ላይ ይተኛል፤እንደ እንስት አንበሳም ያደባል፤ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል?

10. በትረ መንግሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፤የገዥነት ምርኵዝም ከእግሮቹ መካከል።ገዥነት የሚገባው እስኪመጣ ድረስ፣ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙታል።

11. አህያውን በወይን ግንድ፣ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግቅርንጫፍ ላይ ያስራል፤ልብሱን በወይን ጠጅ፣መጐናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል።

12. ዐይኖቹ ከወይን ጠጅ የቀሉ፣ጥርሶቹም ከወተት ይልቅ የነጡ ይሆናሉ።

13. “ዛብሎን፣ በባሕር ዳር ይኖራል፤የመርከቦች መጠጊያም ይሆናል፤ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 49