ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 15:55-58 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

55. እንዲሁም፣ “ሞት ሆይ፤ ድል መንሣትህ የት አለ?ሞት ሆይ፤ መንደፊያህስ የት አለ?”።

56. የሞት መንደፊያ ኀጢአት ነው፤ የኀጢአትም ኀይል ሕግ ነው።

57. ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድልን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።

58. ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ፤ ምክንያቱም ለጌታ የምትደክሙት በከንቱ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 15