ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ቆሮንቶስ 7:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ሚስት አካሏ የራሷ ብቻ አይደለም፤ የባሏም ነው፤ እንዲሁም ባል አካሉ የራሱ ብቻ አይደለም፣ የሚስቱም ነው።

5. በጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በስተቀር፣ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ባለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደ ገና አብራችሁ ሁኑ።

6. ይህን የምለው ግን እንደ ትእዛዝ ሳይሆን እንደ ምክር ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ቆሮንቶስ 7