ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ራእይ 19:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ከዚህ በኋላ የብዙ ሰዎችን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ በሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ሃሌ ሉያ!ማዳን፣ ክብርና ኀይል የአምላካችን ነው፤

2. ፍርዱ እውነትና ጽድቅ ነውና፤በዝሙቷ ምድርን ያረከሰችውን፣ታላቂቱን አመንዝራ ፈርዶባታል፤ስለ አገልጋዮቹም ደም ተበቅሏታል።”

3. ደግሞም እንዲህ አሉ፤“ሃሌ ሉያ!ጢስ ከእርሷ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል።”

4. ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችና አራቱ ሕያዋን ፍጡራን በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው አምላክ ወድቀው ሰገዱ፤ እንዲህም አሉ፤“አሜን፣ ሃሌ ሉያ!”

5. ከዚህ በኋላ እንዲህ የሚል ድምፅ ከዙፋኑ ወጣ፤“እናንተ አገልጋዮቹ ሁሉ፣እርሱን የምትፈሩ፣ታናናሾችና ታላላቆችም፣አምላካችንን አመስግኑ!”

6. ደግሞም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣ እንደ ኀይለኛ ወራጅ ውሃ ድምፅ፣ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ የሚመስል እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ሃሌ ሉያ!ሁሉን ቻይ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።

7. የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ፣የእርሱም ሙሽራ ራሷን ስላዘጋጀች፣ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግክብርም እንስጠው።

8. የሚያንጸባርቅና ንጹሕ፣ከተልባ እግር የተሠራ ቀጭን ልብስ እንድትለብስ ተሰጣት።”ከተልባ እግር የተሠራው ቀጭን ልብስ የቅዱሳን የጽድቅ ሥራ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ራእይ 19