ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሮሜ 2:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለዚህ አንተ በሌላው ላይ የምትፈርድ፣ የምታመካኝበት የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር ሁሉ፣ ራስህን ትኰንናለህ፤ ፈራጅ የሆንኸው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና።

2. እንደዚህ በሚያደርጉትም ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ ትክክለኛ መሆኑን እናውቃለን።

3. እንግዲህ አንተ ሰው በሌሎች ላይ እየፈረድህ፣ ያንኑ የምታደርግ ከሆነ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃል?

4. ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሓ የሚመራህ መሆኑን ሳትገነዘብ፣ የቸርነቱን፣ የቻይነቱን የትዕግሥቱን ባለጠግነት ትንቃለህ?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሮሜ 2