ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤፌሶን 5:12-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. በድብቅ የሚሠሩትን ነገር መናገር ራሱ አሳፋሪ ነውና።

13. ብርሃን የበራበት ነገር ሁሉ ግልጽ ሆኖ ይታያል፤

14. ምክንያቱም ሁሉን ነገር እንዲታይ የሚያደርገው ብርሃን ነውና፤ ስለዚህም፣“አንተ የተኛህ ንቃ፤ከሙታን ተነሣ፤ክርስቶስም ያበራልሃል” ተብሎአል።

15. እንግዲህ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ።

16. ቀኖቹ ክፉ ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ።

17. ስለዚህ ሞኞች አትሁኑ፤ የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ።

18. በመንፈስ ተሞሉ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ፤ ይህ ብክነት ነውና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤፌሶን 5