ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዮሐንስ 7:4-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ራሱን ሊገልጥ እየፈለገ በስውር የሚሠራ ማንም የለምና። አንተም እነዚህን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ፣ ራስህን ለዓለም ግለጥ።”

5. የገዛ ወንድሞቹ እንኳ አላመኑበትም ነበር።

6. ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ለእኔ ትክክለኛው ጊዜ ገና አልደረሰም፤ ለእናንተ ግን ማንኛውም ጊዜ ምቹ ነው።

7. ዓለም እናንተን ሊጠላ አይችልም፤ እኔ ግን፣ አድራጎቱ ክፉ መሆኑን ስለምመሰክርበት ይጠላኛል።

8. እናንተ ወደ በዓሉ ሂዱ፤ ለእኔ ትክክለኛው ጊዜ ስላልደረሰ ወደ በዓሉ አልሄድም።”

9. ይህን ብሎአቸው በገሊላ ቈየ።

10. ይሁን እንጂ፣ ወንድሞቹ ወደ በዓሉ ከሄዱ በኋላ፣ እርሱም በግልጥ ሳይሆን በስውር ወደ በዓሉ ሄደ።

11. በበዓሉም ላይ አይሁድ፣ “ያ ሰው የት አለ?” እያሉ ይፈልጉት ነበር።

12. ስለ እርሱ በሕዝቡ መካከል ብዙ ጒምጒምታ ነበር። አንዳንዶች፣ “ደግ ሰው ነው” አሉ።ሌሎች ግን፣ “የለም፤ ሕዝቡን የሚያስት ነው” አሉ።

13. ይሁን እንጂ አይሁድን ከመፍራት የተነሣ ስለ እርሱ በግልጽ የተናገረ ማንም አልነበረም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዮሐንስ 7