ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. መንገዳቸው ነቀፋ የሌለበት፣ በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው።

2. ምስክርነቱን የሚጠብቁ፣በፍጹምም ልብ የሚሹት የተባረኩ ናቸው፤

3. ዐመፅን አያደርጉም፤ነገር ግን በመንገዱ ይሄዳሉ።

4. ጠንቅቀን እንጠብቃት ዘንድ፣አንተ ሥርዐትን አዘሃል።

5. ሥርዐትህን እጠብቅ ዘንድ፣ምነው መንገዴ ጽኑ በሆነልኝ ኖሮ!

6. ወደ ትእዛዛትህ ስመለከት፣በዚያን ጊዜ አላፍርም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119