ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:10-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. በሙሉ ልቤ ፈለግሁህ፤ከትእዛዛትህ ፈቀቅ እንዳልል አድርገኝ።

11. አንተን እንዳልበድል፣ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።

12. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ቡሩክ ነህ፤ሥርዐትህን አስተምረኝ።

13. ከአንደበትህ የሚወጣውን ደንብ ሁሉ፣በከንፈሬ እናገራለሁ።

14. ሰው በሀብቱ ብዛት ደስ እንደሚለው፣ምስክርነትህን በመከተል ደስ ይለኛል።

15. ድንጋጌህን አሰላስላለሁ፤ልቤን በመንገድህ ላይ ጥያለሁ።

16. በሥርዐትህ ደስ ይለኛል፤ቃልህንም አልዘነጋም።

17. ሕያው እንድሆን፣ ቃልህንም እንድጠብቅ፣ለአገልጋይህ መልካም አድርግ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119