ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:102-107 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

102. አንተው ራስህ አስተምረኸኛልና፣ከድንጋጌህ ዘወር አላልሁም።

103. ቃልህ ለምላሴ ምንኛ ጣፋጭ ነው!ለአፌም ከማር ወለላ ይልቅ ጣዕም አለው።

104. ከመመሪያህ ማስተዋልን አገኘሁ፤ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ።

105. ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ለመንገዴም ብርሃን ነው።

106. የጽድቅ ሕግህን ለመጠበቅ፤ምያለሁ፤ ይህንኑ አጸናለሁ።

107. እጅግ ተቸግሬአለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቃልህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119