ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:107-114 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

107. እጅግ ተቸግሬአለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቃልህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ።

108. እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈቅጄ ያቀረብሁትን የአፌን የምስጋና መሥዋዕት ተቀበል፤ሕግህንም አስተምረኝ።

109. ነፍሴ ዘወትር አደጋ ላይ ናት፤ሕግህን ግን አልረሳሁም።

110. ክፉዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤እኔ ግን መመሪያህን አልተላለፍሁም።

111. ምስክርነትህ የዘላለም ውርሴ ናት፤ልቤ በዚህ ሐሤት ያደርጋልና።

112. ትእዛዝህን ለዘላለም፣ እስከ ወዲያኛው ለመፈጸም፣ልቤን ወደዚያው አዘነበልሁ።

113. መንታ ልብ ያላቸውን ጠላሁ፤ሕግህን ግን ወደድሁ።

114. አንተ መጠጊያዬና ጋሻዬ ነህ፤ቃልህን በተስፋ እጠብቃለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119