ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:124-129 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

124. ለባሪያህ እንደ ምሕረትህ መጠን አድርግ፤ሥርዐትህንም አስተምረኝ።

125. እኔ ባሪያህ ነኝ፤ምስክርነትህን ዐውቅ ዘንድ ማስተዋልን ስጠኝ።

126. እግዚአብሔር ሆይ፤ሕግህ እየተጣሰ ነውና፣ጊዜው አንተ የምትሠራበት ነው።

127. ስለዚህ ከወርቅ፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ፣ትእዛዛትህን ወደድሁ።

128. መመሪያህ ሙሉ በሙሉ ልክ ነው አልሁ፤ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ።

129. ምስክርነትህ ሁሉ ድንቅ ነው፤ስለዚህ ነፍሴ ትጠብቀዋለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119