ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:141-145 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

141. እኔ ታናሽና የተናቅሁ ነኝ፤ነገር ግን መመሪያህን አልዘነጋሁም።

142. ጽድቅህ ዘላለማዊ ጽድቅ ነው፤ሕግህም እውነት ነው።

143. መከራና ሥቃይ ደርሶብኛል፤ነገር ግን ትእዛዝህ ደስታዬ ነው።

144. ምስክርነትህ ለዘላለም የጽድቅ ምስክርነት ነው፤በሕይወት እኖር ዘንድ ማስተዋልን ስጠኝ።

145. እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ እጮኻለሁና መልስልኝ፤ሥርዐትህንም እጠብቃለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119