ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:168-175 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

168. መንገዴ ሁሉ በፊትህ ግልጽ ነውና፣ሕግህንና ምስክርነትህን እጠብቃለሁ።

169. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴ ከፊትህ ይድረስ፤እንደ ቃልህም ማስተዋልን ስጠኝ።

170. ልመናዬ ከፊትህ ይድረስ፤እንደ ቃልህም ታደገኝ።

171. ሥርዐትህን አስተምረኸኛልና፣ከንፈሮቼ ምስጋናን አፈለቁ።

172. ትእዛዛትህ ሁሉ የጽድቅ ትእዛዛት ናቸውና፣አንደበቴ ስለ ቃልህ ይዘምር።

173. ትእዛዝህን መርጫለሁና፣እጅህ እኔን ለመርዳት ዝግጁ ይሁን።

174. እግዚአብሔር ሆይ፤ ማዳንህን ናፈቅሁ፤ሕግህም ደስታዬ ነው።

175. አመሰግንህ ዘንድ በሕይወት ልኑር፤ሕግህም ይርዳኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119