ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:170-176 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

170. ልመናዬ ከፊትህ ይድረስ፤እንደ ቃልህም ታደገኝ።

171. ሥርዐትህን አስተምረኸኛልና፣ከንፈሮቼ ምስጋናን አፈለቁ።

172. ትእዛዛትህ ሁሉ የጽድቅ ትእዛዛት ናቸውና፣አንደበቴ ስለ ቃልህ ይዘምር።

173. ትእዛዝህን መርጫለሁና፣እጅህ እኔን ለመርዳት ዝግጁ ይሁን።

174. እግዚአብሔር ሆይ፤ ማዳንህን ናፈቅሁ፤ሕግህም ደስታዬ ነው።

175. አመሰግንህ ዘንድ በሕይወት ልኑር፤ሕግህም ይርዳኝ።

176. እንደ ጠፋ በግ ተቅበዘበዝሁ፤ትእዛዛትህን አልረሳሁምና፣ባሪያህን ፈልገው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119