ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:26-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. ስለ መንገዴ ገልጬ ነገርሁህ፤ አንተም መለስህልኝ፤ሥርዐትህን አስተምረኝ።

27. የድንጋጌህን መንገድ እንዳስተውል አድርገኝ፤እኔም ድንቅ ሥራህን አሰላስላለሁ።

28. ነፍሴ በሐዘን ተዝለፈለፈች፤እንደ ቃልህ አበርታኝ።

29. የሽንገላን መንገድ ከእኔ አርቅ፤ሕግህን በጸጋህ ስጠኝ።

30. የእውነትን መንገድ መርጫለሁ፤ሕግህንም ፊት ለፊቴ አድርጌአለሁ።

31. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከምስክርነትህ ጋር ተጣብቄአለሁ፤አሳልፈህ ለውርደት አትስጠኝ።

32. ልቤን አስፍተህልኛልና፣በትእዛዛትህ መንገድ እሮጣለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119