ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:40-47 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

40. እነሆ፤ ድንጋጌህን ናፈቅሁ፤በጽድቅህ ሕያው አድርገኝ።

41. እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ወደ እኔ ይምጣ፤ማዳንህም እንደ ቃልህ ይላክልኝ።

42. በቃልህ ታምኛለሁና፣ለሚሰድቡኝ መልስ እሰጣለሁ።

43. ሕግህን ተስፋ አድርጌአለሁና፣የእውነትን ቃል ከአፌ ፈጽመህ አታርቅ።

44. ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ሕግህን ዘወትር እጠብቃለሁ።

45. ሥርዐትህን እሻለሁና፣እንደ ልቤ ወዲያ ወዲህ እመላለሳለሁ።

46. ምስክርነትህን በነገሥታት ፊት እናገራለሁ፤ይህን በማድረግም ዕፍረት አይሰማኝም።

47. እኔ እወደዋለሁና፣በትእዛዝህ ደስ ይለኛል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119