ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:9-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ጒልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል?በቃልህ መሠረት በመኖር ነው።

10. በሙሉ ልቤ ፈለግሁህ፤ከትእዛዛትህ ፈቀቅ እንዳልል አድርገኝ።

11. አንተን እንዳልበድል፣ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።

12. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ቡሩክ ነህ፤ሥርዐትህን አስተምረኝ።

13. ከአንደበትህ የሚወጣውን ደንብ ሁሉ፣በከንፈሬ እናገራለሁ።

14. ሰው በሀብቱ ብዛት ደስ እንደሚለው፣ምስክርነትህን በመከተል ደስ ይለኛል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119