ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 139:7-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ?ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?

8. ወደ ሰማይ ብወጣ፣ አንተ በዚያ አለህ፤መኝታዬንም በሲኦል ባደርግ በዚያ ትገኛለህ።

9. በንጋት ክንፍ ተነሥቼ ብበር፣እስከ ባሕሩ ዳርቻ መጨረሻ ብሄድ፣

10. በዚያም ቢሆን እጅህ ትመራኛለች፤ቀኝ እጅህም አጥብቃ ትይዘኛለች።

11. እኔም፣ “ጨለማው በርግጥ ይሰውረኛል፤በዙሪያዬ ያለውም ብርሃን ሌሊት ይሆናል” ብል፣

12. ጨለማ የአንተን ዐይን አይዝም፤ሌሊቱም እንደ ቀን ያበራል፤ጨለማም ብርሃንም ለአንተ አንድ ናቸውና።

13. አንተ ውስጣዊ ሰውነቴን ፈጥረሃልና፤በእናቴም ማሕፀን ውስጥ አበጃጅተህ ሠራኸኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 139