ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 148:6-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው፤የማይሻርም ሕግ ደነገገላቸው።

7. የባሕር ውስጥ ግዙፍ ፍጥረትና ጥልቅ ውሆች ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑት።

8. እሳትና በረዶ፣ ዐመዳይና ጭጋግ፣ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ፣

9. ተራሮችና ኰረብቶች ሁሉ፣የፍሬ ዛፎችና ዝግቦች ሁሉ፣

10. የዱር አራዊትና የቤት እንስሳት ሁሉ፣በምድር የሚሳቡ ፍጥረታትና የሚበሩ ወፎችም፣

11. የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ፣መሳፍንትና የምድር ገዦች ሁሉ፣

12. ወጣት ወንዶችና ደናግል፣አረጋውያንና ልጆች ያመስግኑት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 148