ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 32:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. መተላለፉ ይቅር የተባለለት፣ኀጢአቱም የተሸፈነለት፣እንዴት ቡሩክ ነው!

2. እግዚአብሔር ኀጢአቱን የማይቈጥርበት፣በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው፣እርሱ ቡሩክ ነው።

3. ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሣ፣ዝም ባልሁ ጊዜ፣ዐጥንቶቼ ተበላሹ፤

4. በቀንና በሌሊት፣እጅህ ከብዳብኛለችና፤ኀይሌም የበጋ ትኵሳት እንደላሰው ነገር፣ከውስጤ ተሟጠጠ። ሴላ

5. ኀጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፤በደሌንም አልሸሸግሁም፤ደግሞም “መተላለፌን ለእግዚአብሔር እናዘዛለሁ” አልሁ፤አንተም የኀጢአቴን በደል፣ይቅር አልህ። ሴላ

6. ስለዚህ ጻድቅ ሁሉ፣በጭንቅ ጊዜ ወደ አንተ ይጸልይ፤ኀይለኛ ጐርፍ አካባቢውን ቢያጥለቀልቅም፣እርሱ አጠገብ አይደርስም።

7. አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤በድል ዝማሬም ትከበኛለህ። ሴላ

8. አስተምርሃለሁ፤ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤እመክርሃለሁ፤ በዐይኔም እከታተልሃለሁ።

9. በልባብና በልጓም ካልተገሩ በቀር፣ወደ አንተ እንደማይቀርቡት፣ማስተዋል እንደሌላቸው፣እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 32