ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 32:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ስለዚህ ጻድቅ ሁሉ፣በጭንቅ ጊዜ ወደ አንተ ይጸልይ፤ኀይለኛ ጐርፍ አካባቢውን ቢያጥለቀልቅም፣እርሱ አጠገብ አይደርስም።

7. አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤በድል ዝማሬም ትከበኛለህ። ሴላ

8. አስተምርሃለሁ፤ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤እመክርሃለሁ፤ በዐይኔም እከታተልሃለሁ።

9. በልባብና በልጓም ካልተገሩ በቀር፣ወደ አንተ እንደማይቀርቡት፣ማስተዋል እንደሌላቸው፣እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።

10. የክፉዎች ዋይታ ብዙ ነው፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን፣ምሕረት ይከበዋል።

11. ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ቅን ልብ ያላችሁም ሁሉ እልል በሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 32