ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 37:11-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤በታላቅ ሰላምም ሐሤት ያደርጋሉ።

12. ክፉዎች በጻድቃን ላይ ያሤራሉ፤ጥርሳቸውንም ያፋጩባቸዋል።

13. እግዚአብሔር ግን ይሥቅባቸዋል፤ቀናቸው እንደ ደረሰ ያውቃልና።

14. ድኾችንና ችግረኞችን ለመጣል፣አካሄዳቸው ቀና የሆነውንም ለመግደል፣ክፉዎች ሰይፋቸውን መዘዙ፤ቀስታቸውንም ገተሩ።

15. ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤ቀስታቸውም ይሰበራል።

16. የጻድቅ ጥቂት ሀብት፣ከክፉዎች ብዙ ጥሪት ይበልጣል።

17. የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና፤ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ደግፎ ይይዛቸዋል።

18. እግዚአብሔር የንጹሐንን የሕይወት ዘመን ያውቃል፤ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል።

19. በክፉ ጊዜ ዐንገት አይደፉም፤በራብ ዘመንም ይጠግባሉ።

20. ክፉዎች ግን ይጠፋሉ፤ የእግዚአብሔር ጠላቶች እንደ መስክ ውበት ይሆናሉ፤ይጠፋሉ፤ እንደ ጢስም ተነው ይጠፋሉ።

21. ኀጢአተኛ ይበደራል፤ መልሶም አይከፍልም፤ጻድቅ ግን ይቸራል።

22. እግዚአብሔር የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ፤እርሱ የሚረግማቸው ግን ይጠፋሉ።

23. የሰው አካሄድ በእግዚአብሔር ይጸናል፤በመንገዱ ደስ ይለዋል።

24. ቢሰናከልም አይወድቅም፤ እግዚአብሔር በእጁ ደግፎ ይይዘዋልና።

25. ጐልማሳ ነበርሁ፤ አሁን አርጅቻለሁ፤ነገር ግን ጻድቅ ሲጣል፣ዘሩም እንጀራ ሲለምን አላየሁም።

26. ሁል ጊዜ ቸር ነው፤ ያበድራልም፤ልጆቹም የተባረኩ ይሆናሉ።

27. ከክፉ ራቅ፤ መልካሙንም አድርግ፤ለዘላለምም ትኖራለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 37