ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 37:21-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ኀጢአተኛ ይበደራል፤ መልሶም አይከፍልም፤ጻድቅ ግን ይቸራል።

22. እግዚአብሔር የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ፤እርሱ የሚረግማቸው ግን ይጠፋሉ።

23. የሰው አካሄድ በእግዚአብሔር ይጸናል፤በመንገዱ ደስ ይለዋል።

24. ቢሰናከልም አይወድቅም፤ እግዚአብሔር በእጁ ደግፎ ይይዘዋልና።

25. ጐልማሳ ነበርሁ፤ አሁን አርጅቻለሁ፤ነገር ግን ጻድቅ ሲጣል፣ዘሩም እንጀራ ሲለምን አላየሁም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 37