ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 84:5-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. አንተን ብርታታቸው ያደረጉ፣በልባቸው የጽዮንን መንገድ የሚያስቡ ቡሩካን ናቸው።

6. በልቅሶ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ፣የምንጭ መፍለቂያ ቦታ ያደርጉታል፤የበልጒም ዝናብ ያረሰርሰዋል።

7. ከኀይል ወደ ኀይል ይሸጋገራሉ፤እያንዳንዱም በጽዮን ባለው አምላክ ፊት ይቀርባል።

8. የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤የያዕቆብ አምላክ ሆይ አድምጠኝ። ሴላ

9. አምላክ ሆይ፤ ጋሻችንን እይልን፤የቀባኸውንም ተመልከት።

10. በሌላ ስፍራ ሺህ ቀን ከመኖር፣በአደባባይህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላል፤በክፉዎች ድንኳን ከመቀመጥ ይልቅ፣በአምላኬ ቤት ደጅ መቆም እመርጣለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 84