ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 6:3-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ክፉውን ቀን ለምታርቁ፣የግፍንም ወንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ!

4. በዝሆን ጥርስ ባጌጠ ዐልጋ ላይ ለምትተኙ፤በድንክ ዐልጋችሁ ላይ ለምትዝናኑ፣ከበጎች መንጋ ጠቦትን፣ከጋጣም ጥጃን ለምትበሉ፤

5. ባልተቃኘ በገና ለምትዘፍኑ፣በሙዚቃ መሣሪያ ለመጫወት ለምትሹ፣

6. በፋጋ የወይን ጠጅ ለምትጠጡ፣ምርጥ ሽቱም ለምትቀቡ፣ስለ ዮሴፍ መከራ ግን ለማታዝኑ ወዮላችሁ!

7. ስለዚህ እናንተ በመጀመሪያ በምርኮ ከሚወሰዱት መካከል ናቸሁ፤መፈንጠዛችሁና መዝናናታችሁም ያበቃል።

8. ጌታእግዚአብሔር “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፤ምሽጎቹንም ጠልቻለሁ፤ከተማዪቱንና በውስጥዋ ያለውን ሁሉ፣አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሎአል፤ይላል የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር።

9. በአንድ ቤት ውስጥ ዐሥር ሰዎች ቢቀሩ እነርሱም ይሞታሉ።

10. በድኖቹንም ከቤት አውጥቶ ማቃጠል ያለበት አንድ ዘመድ መጥቶ ተደብቆ ያለውን ሰው፣ “ከአንተ ጋር የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ሲለው፣ እርሱም “የለም” ይለዋል፤ ከዚያም በኋላ፣ “ዝም በል፤ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አይገባንም” ይለዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 6