ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 8:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. “በዚህ ነገር ምድር አትናወጥምን?በውስጧ የሚኖሩትስ ሁሉ አያለቅሱምን?የምድር ሁለመና እንደ ዐባይ ወንዝ ይነሣል፤እንደ ግብጽ ወንዝም ወደ ላይ ይፈናጠራል፤ተመልሶም ይወርዳል።”

9. ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በዚያ ቀን፣ ፀሐይ በቀትር እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፤ምድርንም ደማቅ ብርሃን ሳለ በቀን አጨልማታለሁ።

10. ዓመት በዓላችሁን ወደ ልቅሶ፣ዝማሬአችሁንም ሁሉ ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ሁላችሁም ማቅ እንድትለብሱ፣ጠጒራችሁንም እንድትላጩ አደርጋለሁ፤ያን ጊዜ ለአንድያ ልጅ ሞት እንደሚለቀስበት፣ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።”

11. ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በምድር ላይ ረሐብን የምሰድበት ዘመን ይመጣል፤ይኸውም የእግዚአብሔርን ቃል የመስማት ረሐብ እንጂ፣እንጀራን የመራብ ወይም ውሃን የመጠማት አይደለም።

12. ሰዎች እግዚአብሔርን ለመሻት፣ከባሕር ወደ ባሕር፣ከሰሜን ወደ ምሥራቅ ይንከራተታሉ፤ነገር ግን አያገኙትም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 8