ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 5:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “በኢየሩሳሌም መንገዶች እስቲ ውጡ፤ ወደ ላይ ወደታችም ውረዱ፤ዙሪያውን ተመልከቱ ቃኙ፤በአደባባይዋም ፈልጉ፤እውነትን የሚሻና በቅንነት የሚሄድ፣አንድ ሰው እንኳ ብታገኙ፣እኔ ይህቺን ከተማ እምራታለሁ።

2. ‘ሕያው እግዚአብሔርን! ቢሉም፣የሚምሉት በሐሰት ነው።”

3. እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህ እውነትን አይመለከቱምን?አንተ መታሃቸው፤ እነርሱ ግን አልተሰማቸውም፤አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን አልታረሙም፤ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠነከሩበንስሓ ለመመለስም አልፈለጉም።

4. እኔም በልቤ እንዲህ አልሁ፤ “እነዚህ ድኾች ናቸው፤ሞኞች ናቸው፤ የእግዚአብሔርን መንገድ፣የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና።

5. ስለዚህ ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ፤ለእነርሱም እናገራለሁ፤በእርግጥ እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድ፣የአምላካቸውንም ሕግ ያውቃሉና።”ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ ያው እንደዚያው ቀንበሩን ሰብረዋል፤እስራቱንም በጥሰዋል።

6. ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰባብራቸዋል፣የበረሓ ተኵላም ይቦጫጭቃቸዋል፤ብቅ የሚለውን ሰው ሁሉ ለመገነጣጠል፣ነብር በከተሞቻቸው ዙሪያ ያደባል፤ዐመፃቸው ታላቅ፣ክሕደታቸው ብዙ ነውና።

7. “ታዲያ፣ እንዴት ይቅር ልልሽ እችላለሁ?ልጆችሽ ትተውኛል፤እውነተኛውን አምላክ ትተው አማልክት ባልሆኑት ምለዋል፤እስኪጠግቡ ድረስ መገብኋቸው፤እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ወደ ጋለሞቶችም ቤት ተንጋጉ።

8. እንደ ተቀለበ ብርቱ ድንጒላ ፈረስ ሆኑ፤እያንዳንዱም የሌላውን ሚስት ተከትሎ አሽካካ።

9. ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀጣቸውምን?”ይላል እግዚአብሔር።“እኔ ራሴ እንደዚህ ዐይነቱን ሕዝብ፣አልበቀልምን?

10. “ወደ ወይን አትክልቷ ስፍራ ገብታችሁ አበላሹት፤ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉት፤ቅርንጫፎቿን ገነጣጥሉ፤ የእግዚአብሔር አይደሉምና፤

11. የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት፣ፈጽመው ከድተውኛል፤”ይላል እግዚአብሔር።

12. በእግዚአብሔር ላይ ሐሰትን ተናገሩ፤እንዲህም አሉ፤ “እሱ ምንም አያደርግም!ክፉ ነገር አይደርስብንም፤ሰይፍም ራብም አናይም፤

13. ነቢያቱ ነፋስ እንጂ ሌላ ነገር አይደሉም፤ቃሉም በውስጣቸው የለም፤ያሉት ሁሉ በእነርሱ ላይ ይመለስ።”

14. ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ሕዝቡ ይህን ቃል ስለ ተናገረ፣ቃሌን በአፍህ ውስጥ የሚፋጅ እሳት፣ይህንም ሕዝብ ማገዶ አደርጋለሁ፤እሳቱም ይበላቸዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 5