ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰባብራቸዋል፣የበረሓ ተኵላም ይቦጫጭቃቸዋል፤ብቅ የሚለውን ሰው ሁሉ ለመገነጣጠል፣ነብር በከተሞቻቸው ዙሪያ ያደባል፤ዐመፃቸው ታላቅ፣ክሕደታቸው ብዙ ነውና።