ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 2:22-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ከዚያም የብንያም ነገድ ይቀጥላል፣ የብንያም ሕዝብ አለቃ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ሲሆን፣

23. የሰራዊቱም ብዛት ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነው።

24. በየሰራዊታቸው ሆነው ከኤፍሬም ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ አንድ መቶ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ናቸው፤ እነዚህ ሦስተኛ ሆነው ይመጣሉ።

25. “በሰሜን በኩል የዳን ምድብ ሰራዊት በዐርማው ሥር ይሆናል፤ የዳን ሕዝብ አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ሲሆን፣

26. የሰራዊቱም ብዛት ሥልሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነው።

27. “የአሴር ነገድ ከእነዚህ ቀጥሎ ይሰፍራል፤ የአሴር ሕዝብ አለቃ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ሲሆን፣

28. የሰራዊቱም ብዛት አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ ነው።

29. ከዚያም የንፍታሌም ነገድ ይቀጥላል፤ የንፍታሌም ሕዝብ አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ሲሆን፣

30. የሰራዊቱም ብዛት አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነው።

31. “በየሰራዊታቸው ሆነው ከዳን ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች ሁሉ አንድ መቶ አምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ናቸው፤ እነርሱም በዐርማቸው ሥር በመጨረሻ ይመጣሉ።

32. በየቤተ ሰባቸው፣ በየምድባቸውና በየሰራዊታቸው የተመዘገቡት እስራኤላውያን ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ናቸው፤

33. ያም ሆኖ ግን እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሌዋውያኑ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር አልተቈጠሩም።

34. ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ በየዐርማውም ሥር የሰፈሩትና፣ እያንዳንዳቸው በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የተጓዙት በዚህ ሁኔታ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 2