ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 7:40-52 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

40. ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣

41. እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ አምስት አውራ በግ፣ አምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የሱሪሰዳይ ልጅ ስለሚኤል ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።

42. በስድስተኛው ቀን የጋድ ሕዝብ አለቃ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ስጦታውን አመጣ፤

43. ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቊርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሰላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣

44. ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣

45. ለሚቃጠል መሥዋዕት፣ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው የበግ ጠቦት፣

46. ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣

47. እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ አምስት አውራ በግ፣ አምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።

48. በሰባተኛው ቀን የኤፍሬም ሕዝብ አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ስጦታውን አመጣ፤

49. ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቊርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣

50. ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣

51. ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው የበግ ጠቦት፣

52. ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 7