ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 7:78-85 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

78. በዐሥራ ሁለተኛው ቀን የንፍታሌም ሕዝብ አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ስጦታውን አመጣ፤

79. ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቊርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣

80. ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣

81. ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣

82. ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣

83. እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ አምስት አውራ በግ፣ አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የዔናን ልጅ አኪሬ ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።

84. መሠዊያው በተቀባ ቀን የእስራኤል አለቆች የመሠዊያውን መቀደስ ምክንያት በማድረግ ያቀረቡአቸው ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፤ ዐሥራ ሁለት የብር ሳሕኖች፣ ዐሥራ ሁለት ከብር የተሠሩ ጐድጓዳ ሳሕኖችና ዐሥራ ሁለት የወርቅ ጭልፋዎች፣

85. እያንዳንዱ የብር ሳሕን መቶ ሠላሳ ሰቅል፣ እያንዳንዱም ጐድጓዳ ሳሕን ሰባ ሰቅል፣ ባጠቃላይም የብር ሳሕኖቹ ክብደት በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል ይመዝን ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 7