ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 46:13-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. የይሳኮር ልጆች፦ቶላ፣ ፉዋ፣ ዮብና ሺምሮን ናቸው፤

14. የዛብሎን ልጆች፦ሴሬድ፣ ኤሎንና ያሕልኤል ናቸው፤

15. እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ሳለ፣ ልያ የወለደችለት ናቸው። ሴቷን ዲናን ጨምሮ፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆቹ ቍጥር ሠላሳ ሦስት ነው።

16. የጋድ ልጆች፦ጽፎን፣ ሐጊ፣ ሹኒ፣ ኤስቦን፣ዔሪ፣ አሮዲና አርኤሊ ናቸው፤

17. የአሴር ልጆች፦ዪምና፣ የሱዋ፣ የሱዊና በሪዓ ናቸው፤እኅታቸውም ሤራሕ ናት፤የበሪዓ ልጆች፦ሐቤርና መልኪኤል ናቸው፤

18. እነዚህ ዐሥራ ስድስት ልጆች ሁሉ፣ ላባ ለልጁ ለልያ ከሰጣት ከዘለፋ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው።

19. የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች፦ዮሴፍና ብንያም ናቸው፤

20. በግብፅም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት፣ ምናሴንና ኤፍሬምን ለዮሴፍ ወለደችለት።

21. የብንያም ልጆች፦ቤላ፣ ቤኬር፣ አስቤል፣ ጌራ፣ ናዕማን፣አኪ፣ ሮስ፣ ማንፌንሑፊምና አርድ ናቸው።

22. እነዚህ ዐሥራ አራቱ፣ ራሔል ለያዕቆብ የወለደችለት ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው።

23. የዳን ልጅ፦ሑሺም ነው፤

24. የንፍታሌም ልጆች፦ያሕጽኤል፣ ጉኒ፣ ዬጽርና ሺሌም ናቸው፤

25. እነዚህ ሰባቱ ልጆች ሁሉ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው።

26. ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የሄዱት የገዛ ዘሮቹ ብዛት ሥልሳ ስድስት ሲሆን ይህ ቍጥር ግን የልጆቹን ሚስቶች አይጨምርም።

27. ዮሴፍ በግብፅ የወለዳቸውን ሁለት ልጆች ጨምሮ፣ ወደ ግብፅ የወረደው የያዕቆብ ቤተ ሰብ ቍጥር ሰባ ነበር።

28. ያዕቆብም ወደ ጌሤም ለመሄድ መመሪያን ይቀበል ዘንድ፣ ይሁዳን አስቀድሞ ወደ ዮሴፍ ላከው። እነርሱም ጌሤም ሲደርሱ፣

29. ዮሴፍ ሠረገላውን አዘጋጅቶ፤ አባቱን እስራኤልን ለመቀበል ወደ ጌሤም አመራ።ዮሴፍ አባቱ ዘንድ እንደ ደረሰ፣ ዐንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ለረጅም ጊዜ አለቀሰ።

30. እስራኤልም ዮሴፍን፣ “በሕይወት መኖርህን ስላየሁ፣ ከእንግዲህ ብሞትም አይቈጨኝ” አለው።

31. ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ወደ ፈርዖን ወጥቼ አናግረዋለሁ፤ እንዲህም እለዋለሁ፣ ‘በከነዓን ምድር የሚኖሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል።

32. ሰዎቹ ከብት የሚጠብቁ ስለሆኑ እረኞች ናቸው፤ ሲመጡም በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውንና ከብቶቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው መጥተዋል።’

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 46