ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 48:5-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. “ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ የወለድሃቸው ሁለቱ ልጆችህ ከእንግዲህ የእኔ ልጆች ሆነው ይቈጠራሉ፤ ሮቤልና ስምዖን ልጆቼ እንደሆኑ ሁሉ፣ ኤፍሬምና ምናሴም ልጆቼ ይሆናሉ።

6. ከእነርሱ በኋላ የሚወለዱልህ ልጆች ግን፣ የአንተ ይሁኑ፤ በርስት ድልድላቸው ግን በወንድሞቻቸው ስም ይቈጠራሉ።

7. ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ መልስ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረኝ፣ እናትህ ራሔል በከነዓን ምድር ሞታብኝ ዐዘንሁ። እኔም ወደ ኤፍራታ ማለት ወደ ቤተ ልሔም በሚወስደው መንገድ ዳር ቀበርኋት።”

8. እስራኤልም የዮሴፍን ልጆች ባየ ጊዜ፣“እነዚህ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀ፤

9. ዮሴፍም፣ “እነዚህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ብሎ ለአባቱ መለሰለት፤ እስራኤልም፣ “አቅርባቸውና ልመርቃቸው” አለ።

10. በዚህ ጊዜ እስራኤል ዐይኖቹ በእርጅና ምክንያት በመድከማቸው አጥርቶ ማየት ይሳነው ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን አባቱ ዘንድ አቀረባቸው፤ አባቱም ስሞ ዐቀፋቸው።

11. እስራኤልም ዮሴፍን፣ “ዐይንህን እንደ ገና ዐያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ግን ልጆችህን ጭምር ለማየት አበቃኝ” አለው።

12. ዮሴፍም ልጆቹን ከእስራኤል ጒልበት ፈቀቅ በማድረግ አጐንብሶ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ።

13. ከዚያም ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ኤፍሬምን ከራሱ በስተ ቀኝ፣ ከእስራኤል በስተ ግራ፣ ምናሴን ደግሞ ከራሱ በስተ ግራ፣ ከእስራኤል በስተ ቀኝ በኩል አቀረባቸው።

14. እስራኤል ግን ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረ፤ ግራ እጁንም በቀኝ እጁ ላይ አስተላልፎ በበኵሩ በምናሴ ራስ ላይ አኖረ።

15. ከዚህ በኋላ ዮሴፍን ባረከ፤ እንዲህም አለው፤“አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱየተመላለሱት እግዚአብሔር (ኤሎሂም)፣ለእኔም እስከ ዛሬ ድረስበዘመኔ ሁሉ እረኛ የሆነኝ አምላክ (ኤሎሂም)፣

16. ከጒዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤እነርሱም በስሜ፣በአባቶቼ በአብርሃምናበይስሐቅ ስም ይጠሩ፤በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።

17. ዮሴፍ፣ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማድረጉን ሲያይ ተከፋ፤ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንሥቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤

18. ዮሴፍም፣ “አባቴ ሆይ፤ እንዲህ አይደለም በኵሩ ይህኛው ስለ ሆነ፣ ቀኝ እጅህን እርሱ ራስ ላይ አድርግ” አለው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 48